የበጀት፣ ፋይናንስና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
1.1 የክልሉ የበጀት፣ ፋናንስና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተሏቸዉ ቢሮዎች
ሀ.ፋይናንስ ቢሮ
ለ.የገቢዎች ባለሥልጣን
ሐ. የፕላንና ልማት ቢሮ
መ. ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሲሆን እንዲሁም ይህ ኮሚቴ ለሚከታተለዉ ቢሮ ተጠሪ የሆኑ ተቋማትንም ያጠቃልላል፡፡
1.2 የክልሉ የበጀት፣ ፋናንስና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
- በምክር ቤቱ ለክልሉ መንግሥት የተመደበ ማንኛውም በጀት በአግ ባቡ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
- ኮሚቴው የዋና ኦዲተር ሪፖርትን ይመረምራል፡፡ በሚመረምርበት ወቅትም፤
- የተመደበው በጀት ለታለመለት ዓላማና አገልግሎት ወጪ የተደረገ መሆኑን፣
- ወጪው ስልጣን ባለው አካል የተረጋገጠ መሆኑን፣
- የበጀት ዝውውር ሲኖር በፋይናንስ ሕጉ መሠረት መከናወኑን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
- በምክር ቤቱ ትዕዛዝ በዋና ኦዲት መ/ቤት የተከናወነ የንብረት ኦዲት ውጤትን ይገመግማል
- በማንኛውም መንግሥታዊ አካል በበጀት አመቱ ከተመደበው በላይ የበጀት አጠቃቀም ሲኖር ኮሚቴው ከበጀት በላይ ለማውጣት አስገዳጅ የሆነውን ምክንያት የማጣራትና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘውም ሪፖርትና የውሣኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት፡፡
- ከኮሚቴው ተግባር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የክልሉን ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ኘሮግራሞችና ዕቅዶች በአግባቡ ሥራ ላይ መዋላቸውን ይቆጣጠራል፡፡ ይከታተላል፡፡
- የክልሉ መንግሥት ዓመታዊና ተጨማሪ በጀት በአግባቡ መጽደቁን እና ሥራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፡፡
- የክልሉ መንግሥት ገንዘብና ንብረት በአግባቡ መሰብሰቡን እና መጠበቁን መከታተል፡፡
- ለክልሉ ከፌዴራል የሚሰጡ ድጎማዎችና ክልሉ ለዞንና ልዩ ወረዳ የሚሰጠው የበጀት ድጎማ በቀመሩ መሠረት መሆኑን ይከታተላል፡፡
- በክልሉ ለታችኛዉ የአስተዳደር ዕርከን ዓመታዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ያዘጋጃል፤ለክልሉ ምክር ቤት እንዲጸድቅ ያቀርባል፡፡
- የክልሉን ካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፤ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት አግባብነት ላላቸዉ አካላት ያቀርባል፡፡
- የክልሉን ዓመታዊ የሀብት ግመታ ሰነድ ያዘጋጃል፤ለክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት በማቅርብ ያስፀድቃል፡፡