የከተማና መሠረተ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
1.1 የከተማና መሠረተ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተሏቸዉ ቢሮዎች
ሀ.የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ
ለ. የከተማ ልማትና ኮንስተራክሽን ቢሮ
ሐ.ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
መ.የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ሲሆን እንዲሁም ይህ ኮሚቴ ለሚከታተለዉ ቢሮ ተጠሪ የሆኑ ተቋማትንም ያጠቃልላል፡፡
1.2 የከተማና መሠረተ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከተሉት ተግባራትን ያከናውናል፡፡
1.2.1 የንግድና ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች የክልሉን ዕድገት በሚያፋጥን መልኩ ተግባራዊ መሆኑን፣
1.2.2የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት፣የኢንቨስትመንት ፣ሌሎች የመሠረተ ልማት፪ ፖሊሲዎች ህጎች፣ፕሮግራሞችና ዕቅዶች በተገቢው መንገድ መፈፀማቸውን
1.2.3 ቀልጣፋና ከትራፊክ አደጋ ነፃ የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት ህብረተሰቡ ማግኘቱን
1.2.4 በክልሉ የመሠረተ ልማት አውታሮች አቅርቦት ፣ዕድገትና ሥርጭት ፍትሀዊነት የተረጋገጠ መሆኑ፣
1.2.5 በክልሉ የሚገነቡ ማንኛውም መሠረተ ልማቶች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆናቸውን
1.2.6 በክልሉ ውስጥ የሚከናወኑ መሠረተ ልማቶች ህዝቡን ያሳተፉ፣ ግልፀኝነትንና ተጠያቂነትን የሚያሳትፉ መሆናቸው
1.2.7 ለመሠረተ ልማት አገልግሎት የሚውሉ የካፒታል በጀት በአግባቡ በስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል
1.2.8 የክልሉን ኮንስትራክሽን ስራዎች ይከታተላል
1.2.9 ሌሎች በኮሚቴው ሥር የተደለደሉ መስሪያ ቤቶች ዓላማና ተልኮውን መሠረት በማድረግ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ የአፈፃፀም ሪፖርትም ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡