የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
1.1 የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተሏቸዉን ቢሮዎች
ሀ. ትምህርት ቢሮ
ለ. ጤና ቢሮ
ሐ.ፐብሊክ ሰርቭና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ
መ.ሴቶች፤ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ረ.ባህል፣ ቱርዝምና ስፖርት ቢሮ ሲሆን እንዲሁም ይህ ኮሚቴ ለሚከታተለዉ ቢሮ ተጠሪ የሆኑ ተቋማትንም ያጠቃልላል፡፡
1.2 የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከተሉት ተግባራትን ያከናውናል፡-
- በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉትን የሴቶች መብት መከበራቸውና በመብቶቻቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን መከታተልና መቆጣጠር
- ሴቶችን፣ሕፃናትንና ወጣቶችን የሚጨቁኑ ሕጎች መመርመርና እንዲሻሻሉ ማድረግ፣አዳዲስ የሕግ ሃሳቦችን ማመንጨት
- ሕጎችና ዕቅዶች ሲወጡና ሲፀድቁ የፆታ አድሎን ያስወገዱና ሥር- ዓተ ጾታን ያገናዘቡ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
- በፖለቲካ፣በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥትና በግል ተቋማት ሴቶች ከወንዶች እኩል ተወዳዳሪና ተሣታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል፣ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ጠባሳ ማረም የሚያስችሉ ልዩ የድጋፍ እርምጃ ተጠቃሚ የሚሆኑብት መንገድ ማመቻቸት፣
- ሴቶች ንብረት የማፍራት፣የማስተዳደርና የመቆጣጠር፣የመጠቀም የማስተላለፍና የማውረስ መብቶቻቸው መከበሩን መከታተልና መቆጣጠር፣
- ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች በክልላዊ ልማት ፖሊሲዎች፣ዕቅዶችና በኘሮጀክቶች ዝግጅትና አፈፃፀም በተለይ የሴቶችን ጥቅም የሚነኩ ኘሮጀክቶች ላይ ሐሳባቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲሰጡ ለማስቻል የሴቶች ጉዳይ ፖሊሲ በተለያዩ መንግሥታዊ ድርጅቶች ውስጥ በአጠቃላይ በክልል ደረጃ በተግባር እንዲተረጎምና እየተተረጎመ መሆኑን መቆጣጠር፣
- ሴቶችን፣ሕፃናትና ወጣቶች ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ተጽዕኖ ለማላቀቅ ሴቶችን የሚጨቁኑ በአካላቸው ወይም በአእምሯቸው ላይ ጉዳት የሚያደርሱትን ሕጎች፣ወጎችና ልምዶችን መከላከልና መቆጣጠር
- ሴቶች በእርግዝናና በወሊድ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት መከላከልና ጤንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት መረጃ አቅም የማግኘት መብትን መከታተልና መቆጣጠር፣
- ሴቶችና ወጣቶች በጥያቄዎቻቸው ዙሪያ እንደ ፍላጎታቸዉና እንደ ችግራቸው ዓይነት ተደራጅተው ችግሮቻቸውን ለማስወገድ እንዲታገሉ መብታቸውን እንዲያስከብሩ ድጋፍ መስጠት፣
- በአጠቃላይ የክልሉ መንግሥት የሚያደርገው እንቅስቃሴ የሴቶችን እኩል ተሣታፊነትና ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እንዲሆን ለማስቻል በሕገ መንግሥቱ፣በሕግና በሴክተር ፖሊሲዎች መሠረት መከናወኑን መከታተልና መቆጣጠር፣
- በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጡ መብቶች መከበራቸውን፣ ሕፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰዱበት ጊዜ በመንግሥታዊ ወይም በግል የበጎ አድራጎት ተቋሞች፣ በፍርድ ቤቶች የሕፃናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰባቸውን እና የሕፃናት ደህንነታቸውንና ትምህርታቸውን የሚያራምዱ ተቋሞች መመስረታቸውን ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፡፡
- የወጣቶችና ስፖርት ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣ ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች በአግባቡ በስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፡
- ፈጣን ልማት ለማምጣትና በዴሞክራሲ የታነፀ ህብረተሰበ ለመፍ ጠር በብቃት፣በጥራት፣ በታማኝነትና በቁርጠኝነት ሊሠራ የሚችል የሰለጠነ የሰው ሃይል በአጭር ጊዜና በሰፊው ለማፍራት የሚደረገውን እንቅስቃሴ መከታተልና መቆጣጠር
- የክልሉን አጠቃላይ የማህበራዊ ልማት፣ የትምህርት፣ የጤና፣ የፕሬስ፣ የባህል፣የአቅም ግንባታ እና ሌሎች ፖሊሲዎች፣ ሕጐች፣ ስትራቴጂዎች እና ዕቅዶች በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ይመረምራል፡፡ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡
- ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ተጠብቀው፤ለትውልድ የሚተላለፍበት መንገድ መቀየሱንና ተግባራዊ መሆኑን መከታተልና መቆጣጠር
- ለክልሉ የቱሪዝም ምንጭነት የሚያገለግሉ አስፈላጊ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን መከታተል፣
- የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ሥርጭትን ለመግታት የሚረዱ እንቅስቃሴ ዎችን መከታተልና መቆጣጠር፣
- 18. የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎቶችን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ የአረጋውያን፣ የአካል ጉዳተኞች፣ እና ሥራ አጥነትና ሌሎች የማህበሪዊ ነክ ጉዳዮች አፈፃፀምን መከታተልና መቆጣጠር፣
- የመማሪያ ማስተማሪ ሥራ በአግባቡ መከናወኑን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡
- በክልሉ ዕድሜያቸዉ ለትምህርት የደረሱ ህጻናትና ወጣቶች የመማር ዕድል የሚያገኙበትን ስልት መመቀየሱን ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፡፡
- የቅድመ መደበኛ፣የልዩ ፍላጎት፣የጎልማሶችና የአማራጭ መሠረታዊ ትምህርቶችን አደረጃጀት መወሰናቸዉን ይከታተላል፣ድጋፍ ማድረጋቸዉን ይቆጣጠራል፡
- ሌሎች በኮሚቴው ስር የተደለደሉ መስሪያ ቤቶች ዓላማና ተልኮውን መሠረት በማድረግ አስፈላጊውን የክትትልና የቁጥጥር ሥራ ያከናውናል፡፡