Skip to main content

    የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የግብርናና የገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተሏቸዉ ቢሮዎች

ሀ የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ

ለ. የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ

ሐ. የዉሀ ማእድንና ኤነርጂ ቢሮ ሲሆን ተጠሪ የሆኑ ተቋማትንም ያጠቃልላል፡፡

የግብርናና የገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከተሉት ተግባራትን ያከናውናል፡፡

  • የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ  ምርትና  ምርታማነት እንዲያድግ እና የክልሉን በምግብ እህል ራስን የመቻልና የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ዓላማ ግቡን እየመታ መሆኑን፣
  • የክልሉ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃና እንክብካቤ እየተደረገ የአካባቢ ደህንንት ተጠብቆ ለዘላቂ ልማት እየዋለ መሆኑን
  • በአጠቃላይ ክልሉ የእንስሳት ጤና አግልግሎት፣ የገበያ መሠረት ልማት፣የመኖና የውሀ አቅርቦት እንዲሁም የኤክስቴንሽን ድጋፍ እንዲኖር መደረጉን የሚያደርገውን አፈፃፀም መከታተልና መቆጣጠር፣
  • አርሶ አደሩ ላመረተው ምርት ተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኝበት ሁኔታ ማመቻቸቱን፣
  • የውሃ ማዕድንና የኢነርጂ ልማት አጠቃቀም፣ ተደራሽነትንና ፍትሀዊነትን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ሌሎች በኮሚቴው ስር
  • የተደለደሉ መስሪያ ቤቶች ዓላማና ተልዕኮ መሠረት በማድረግ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ የአፈፃፀሙ ሪፖርት ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡