የሕግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
1.1 የሕግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተሏቸዉ መስሪያ ቤቶች
ሀ.ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ
ለ.ፍትህ ቢሮ
ሐ.ጠቅላይ ፍርድ ቤት
መ.የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት
ሠ.ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት
ረ. የስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሲሆን እንዲሁም ይህ ኮሚቴ ለሚከታተለዉ ቢሮ ተጠሪ የሆኑ ተቋማትንም ያጠቃልላል፡፡
1.2 የሕግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡-
- የክልሉን መንግሥት የፍትህና አስተዳደራዊ አሠራሮች ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማድረግ መደራጀታቸውንና መፈፀማቸውን መከታተልና መቆጣጠር
- በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ መብቶችና ነፃነቶች በአግባቡ መተግበራቸውን መከታተልና መቆጣጠር
- ሕብረተሰቡ ነፃ፣ፍትሃዊና ቀልጣፋ የፍትህ አገልግሎት ማግኘቱን፣
- ሙስናና ብልሹ አሠራርን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት በአግባቡ መደራጀቱን መከታተልና እና መቆጣጠር
- የፍትህና የአስተዳደር ፖሊሲዎች፣ሕጐች፣ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች በአግባቡ በሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተልና መቆጣጠር
- አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ምክር ቤቱ ወደ ማንኛውም ቋሚ ኮሚቴ የሚመራውን ረቂቅ ሕጎች እና ስምምነቶች የሕግ ይዘቱን መመርመር፣
- በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፵፯/፮/ የተመለከተውን የሕግ ከለላ የማንሣት እንደዚሁም ሌሎች የአባላት መብትና ሥነ ምግባር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ይመረምራል፡
- በርዕስ መስተዳደር ጽህፈት ቤት በተለያዩ ዘርፎች የታቀዱ ተግባራቶች በአግባበቡ ሥራ ላይ መዋላቸዉን ይከታተላ፣ይቆጣጠራል
- የምክር ቤቱን ቃለ ጉባዔዎችና ውሳኔዎች፣ ሰነዶች ተመዝግበው እንዲያዙና እንዲጠበቁ ያደርጋል፡፡
- ምክር ቤቱ በየጊዜው የሚያወጣቸው ህጎች በአፊን ጋዜጣ እንዲታተሙ ያደርጋል
- የክልሉን ምክር ቤት ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች አቅም የሚያጎለብትበትን ስልት ይቀይሳል፡፡
- ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡