ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ
የሲዳማ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ
ለመላዉ ሃገራችንና ክልላችን ህዝቦች እንኳን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስረታ 2ኛ አመት በዓል ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ቀን አደረሳችሁ እያልኩ በራሴና በሰፍዉ ሲዳማ ህዝብ ስም ላቅ ያለ ምሰጋና ለማቅረብ እወዳለሁኝ!!
የሲዳማ ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ጥያቄ የህዝብ ትግል የተደረገበት የብሔሩ ተዎላጆች ብዙኋኑ ለሞት፣ ለአካል ጉዳት፣ ሀገርን ለቆ ለመስደድ፣ ለብዙ እንግልት እየተደረገበት ከ130 ዓመት በላይ የቆየ ሲሆን በ2010 ዓ.ም መላዉ የህዝባችን እልህ አስጨራሽ ትግል አድርጕዉ በሐምሌ 11/2010 ምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምጽ ጸድቀዉ ጥያቄዉ ለደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል ምክር ቤት ቀርበዉ ከብዙ ዉጣ ዉረድ እና ትግል በኋላ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ኅዳር 10/2012 ዓ.ም የሀገራችን ህገ-መንግስት አሰራር በጠበቀ መልኩ የህዝብ ሪፈረንደም ተደርጎ ህዝቡ በምርጫዉ 97.7% በራሱ ክልል መሰተዳደር የመሆንን ምርጫ በመምረጡ ሰኔ 11/2012 ዓ.ም የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል ምክር ቤትም ስልጣኑን በይፋ በማስረከቡ ኢፌዲሪ ዴረሽን ም/ቤት የኢፌዲሪ አባል ክልል ሆኖ ኢንዲመዘገብ መቀበሉ የኢትዮጵያ 10ኛ ክልል በመሆን ሰኔ 27/2012 ዓ.ም ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን በ190 ምክር ቤት አባላት በይፋ ከተመሰረተ እነሆ 2ኛ ዓመት ሆነዋል፡፡
የክልሉ ም/ቤት በሁለት ዓመት ዉስጥ ህዝቡን ተጠቃም የሚያደርጉ በርካታ የክልሉ መንግስት ህገ- መንግስት የተለያዩ አዋጆችና መመሪያዎች እንሁም የ10 (አስር) ዓመት የማህበራዊ፣ እኮኖሚያዊ፣ ፖለትካዊና በልማት ተጠቃም የሚያደርግ መሪ ዕቅድ በም/ቤታችን ጸድቀዉ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በህገ- መንግስቱ መሰረት ሶስቱንም የመንግስት አካላትን በማቋቋም እንድሁም ሲዳማ ማንነቱን ከፍ የሚያደርጉ ይህ ነዉ የማይባል ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ሲዳማ የራሱን ባንድራ፣ መዝሙር ባህሉንና ቋንቋዉን እንድሁም ህዝባችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ መሠረተ-ልማቶችን እየተሰሩ መሆኑን በም/ቤታችን በየጊዜ በሚቀርቡ ሪፖርቶችና በቋሚ ኮሚቴዎች ክትትልና ቁጥጥር ለማረጋገጥ ችለናል፡፡
ክልላችን ሰላምና ፀጥታ በመስፈኑ ለመኖሪያ፣ ለመዝናናት፣ለኢንቨስትሜንት ተመራጭ ክልል እየሆነ በመምጣቱ የክልሉ ገቢ የማምንጨት አቅሙ ከፍ ብሏዋል፡፡
ክልል ም/ቤታችን ከተቋቋመ ትንሽ ጊዜ ብሆንም ለሎች አቻ ክልሎች ልምድ ለማካፈል በቅቷል፣ ለአብነት ለድሬ-ዳዋ አስተዳደር ም/ቤትና ለደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ም/ቤት ልምድ አካፍሏል፡፡
የዴሞክራስ ግንባታ ሥራ እንዲጎለበት በየደረጃዉ የሚሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች የህዝቡን ተሳታፍነትና ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እና የአገልግሎት አሠጣጥ ላይ የሚታዩ እንግልት እንድታረሙ ለሚመለከታቸዉ አካላት ዉሳኔ አስተላልፈናል፡፡
በመጨረሻም፣ የክልሉን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ በየደረጃ ያሉ የም/ቤት አባላት አቅም እንድጎለበትና ወቅቱ የሚፈልገዉን ተሳትፎ በማድረግ ህግ፣ደንብና መመሪያ ተከብሮ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ስራቸዉን አጠንክረዉ እንዲሰሩ በማዲረግ የወጣትና የሴቶች የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና ፖለትካዊ ተሳትፎአቸዉንና ተጠቃሚነታቸዉ እንዲጎለበት የምክር ቤት አባላት የሚፈለገዉ ሚናቸዉ እንድወጡና የክልለላችን ብሎም የሃገራችን ዜጎች በሙሉ በሰላም፣ በፍትሃዊነትና በእኩልነት እንድሁም በልማትና በመልካም አስተዳደር እርካታ እንድያገኙ ሁላችንም የበኩላችንን እንድንወጣ እንድሁም ህዝቡን የሚያለያዩ አጀንዳዎች ጥግ እንይዙ አድርገን የክልላችን ብልጽግና እንድረጋገጥ መረባረብ አለብን እያልኩ በአደራ ጭምር መልዕክተን አስተላልፋለሁኝ፡፡
በድጋም እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ!!
ፈጣሪ ሀገራችንን ይባርክ!!