Skip to main content

                አንቀጽ ፬. የምክር ቤቱ ዋና ዋና ሥልጣንና ተግባራት

  1. ምክር ቤቱ በህገ-መንግሥት አንቀጽ 48 የተዘረዘሩት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

 ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ ህገ-መንግስት እንደተነገገው /ቤቱ የክልሉን የውስጥ ጉዳየችን በሚመለከት የበላይ የፖሊትካ ስልጣን ባለቤት ነው፡፡

       ለ) የተለያዩ ልዩ ልዩ ሕጎችን ያወጣል፥

       ሐ) በክልል ውስጥ ተጨማሪ የአስተዳደር እርከኖችን ያቋቁማል፥

       መ) በምክር በቱ አባላት አፌ-ጉባዔና ምክትል አፌ-ጉባኤ ይመረጣል፥

       ሠ) ለምክር ቤቱ ሥራ የሚያስፈልጉ ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎችን ይሰይማል፥

       ረ) ከምክር ቤቱ  አባላት መካከል በርዕሰ መስተዳድሩን በምርጫ ይሰይማል፥

       ሰ) በርዕሰ መስተዳድሩ አቅራቢነት የክልሉን መስተዳድር ምክር ቤት አባላት ሹመት ያፀድቃል፥

       ሸ) በርዕሰ መስተዳድሩ አቅራቢነት የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ፕሬዝዳንት፥ ምክትል ፕሬዝዳንት፥ ዋና ኦድተሩንና ምክትል ዋና ኦድተሩን ይሾማል፥

      ቀ)  የክልሉን ጠቅላይ ፥ ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶችን ያቋቁማል፥ ዳኞችን ይሾማል፥

      በ) የክልሉን በጀት ምርምር ያፀድቃል፥

ተ) የክልል መስተዳድሩን የሠራተኛ አስተዳድርና የሥራ ሁኔታዎችን በተመለከተ ህግ ያወጣም፥

ቸ) የአስቾካይ ጊዜ አዋጅ ምርምር ያፀድቃል፥

 ኀ) የክልሉን በርዕሰ መስተዳድና ለሎች የክልሉን መንግስት ባለስልጣንት ለጥያቄ የጠራል፥ የመስተዳድር ምክር ቤት የስራ እንቅስቃሴንና አሰራርን ይመረምራል

  ) ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዙ ሁኔታዎችን በመፈጠር ግልፀኝነት፣ ተጠያቂነትና አሳታፊነት መርህን በመከተል ይሠራል፡፡

     ኘ) የክልሉን ህገ-መንግስት ያሻሽላል፡፡

      ዐ) አቤቱታዎችን፤ጥቆማና ቅሬታ ይቀበላ፤ ያዳምጣል፤እንዲሁም ምላሽ ይሠጣል፡፡

  1. ምክር ቤቱ ይህን ደንብ ለማስፈጸም በዚህ ደንብ አንቀጽ 4 የተዘረዘሩ ተግባራቶችን ለመፈጸም የሚከተሉ መርሆችን መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡

1. በአጭርና ረጅም ጊዜ ዕቅድ መመራት

2. ለተግባራት ዉጤታማነት የሚረዱ ምቹ የሥራ ሁኔታ በመፍጠር የግልጽነት፤ የተጠያቂነትና የአሳታፊነት መርህን በመከተል፤ ተግባራትን በመገምገም

4. ከላ በተገለፀወው መሰረት የዘረዘሩ ተግባራቶችንና መርሆዎች እንደሁኔታ በምክር ቤቱ ከተቋቋሙ ኮሚቴዎች ሥራ ጋር ተጣጥመዉ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡